Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጉባኤው የሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የህብረቱ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት ጉባኤው በኮቪድ-19 ምክንያት ባለፉት ሁለት አመታት አለመካሄዱን ተናግረዋል።

ህብረቱ በሚንቀሳቀስበት በጀትና የፋይናንስ ድጋፍ ዙሪያም ውሳኔዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

ዛሬና ነገ የሚካሄደው ስብሰባ የሀገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የምጣኔ ሀብት ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት ነው።

በ2022 የምግብ ዋስትናን ስለማረጋገጥ፣ በአጋሮች ድጋፍ ያልተንጠለጠለ ራስን ስለመቻል፣ የአህጉሩን ምጣኔ ሀብት ስለማስተሳሰር መስራት ይገባል ብለዋል ሙሳ ፋቂ መሃማት።

አፍሪካ አህጉር በኮቪድ 19 እየተፈተነችበት ያለው ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት የወቅቱ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር ክርስቶፌ ሉቱንዱላ እኒህን ፈተናዎች የሚያሻግሩ ሀሳቦች ሀሳቦችን ማንሳት ይገባል ነው ያሉት።

አጀንዳ 2063ን ለመተገበር እየተኬደበት ያለው መንገድ፣ ኮቪድንና ሌሎች ፈተናዎችን የተቋቋመ ጠንካራ ሀገር ስለመገንባት፣ የአህጉሪቱን ሰላምና ደህንነት ስለመጠበቅ መስራትና መወያየት ይገባል ነው ያሉት።

የአፍሪካ ሀገራት የባለብዙ ዘርፍ ትብብራቸውን ማሳደግ ይገባል በተባለበት የህብረቱ መክፈቻ ስነስርዓት ትብብራቸውን የሚያሳድግ ፍኖተ ካርታን ቀርፆ መተግበር ይገባል ተብሏል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.