Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕከተኞች ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ በህብረቱ ዋና ፅህፈት ቤት ተጀመረ።
በመደበኛ ጉባኤው ላይ የህብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
 
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤውም “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው።
 
በጉባኤያቸውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በዚሁ አዲስ አበባ ለሚካሄደው ለህብረቱ ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ አጀንዳዎችን የሚያረቅ ይሆናል።
 
36ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤቱ ጉባኤ በፈረንጆቹ የካቲት 6 እና 7 2020 ይካሄዳል።
 
በመቀጠልም በተመሳሳይ መሪ ቃል የካቲት 9 እና 10 ቀን 2020 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚካሄድ ይሆናል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.