Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ከዛሬ ጀምሮ ችግኝ እንዲተክሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ ችግኝ እንዲተክሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት አራተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ የእጽዋት ማዕከል ተጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መኸመትእና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባደረጉት ንግግር÷ ላላፉት አራት ዓመታት በስኬት ሲከናወን የቆየው አረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ ትልልቅ ነገሮችን መጀመር ብቻ ሳይሆን የምትጨርስ ሀገር እንደሆነች ለዓለም ያሳየችበት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ከዛሬ ጀምሮ ችግኝ እንዲተክሉ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ÷ አንድ ሰው በሁለት ወራት ውስጥ 100 ችግኞች የመትከል ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ።

በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው÷ በዚህ ዓመት “አረንጓዴ ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል ስድስት ቢሊየን ችግኝ እንደሚተከል ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ አስመልክተው ባወጡት መግለጫ፥ በዚህ ዓመት በአጠቃላይ በአራት ዓመቱ መርሐ ግብር ለማሳካት የታቀደው 20 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ እንደሚሳካ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት አመታት በሶስት ዙር 20 ሚሊየን ዜጎችን በማሳተፍ 18 ቢሊየን ችግኞች መተከሉ ተገልጿል።

በዓልአዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.