Fana: At a Speed of Life!

40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕላቲኒየም ደረጃ በተሠጠው በ40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ  ሲደርሱም አቀባበል  ተደርጎላቸዋል ።

በአቀባበሉ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ማርቆስ ገነቲና  የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ  መገኘታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።።

በለንደን ማራቶን አትሌት ሹራ ቅጣታ ቶላ በ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ አትሌት ሲሳይ ለማ ሶስተኛ ደረጃን ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

አትሌት ሞስነት ገረመው ፣ አትሌት ሙሌ ዋሲሁን እና  አትሌት ታምራት ቶላ ከ4 እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃን ይዘው  በማጠናቀቃቸው እንዲሁ ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.