Fana: At a Speed of Life!

40 ጎራሽ የጦር መሳሪያ ከወዳደቁ ብረቶች የሰራው ወጣት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አብነት ወዳጀ ይባላል፤ ይህ የ18 ዓመት ወጣት የጎንደር ከተማ ነዋሪ ሲሆን፥ ከልጅነቱ ጀምሮ ከካርቶንና ከወዳደቁ ነገሮች የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ይስራ ነበር፡፡

ወጣቱ በአሁኑ ወቅት አገር በውስጥና በውጭ ባንዳዎች የተከፈተባትን መልከ ብዙ ጦርነት ለመመከት የጦር መሳሪያ አስፈላጊ ነው ብሎ በማመኑ ከወዳደቁ ብራቶች በመገጣጠም ‘ቺቺ’ ብሎ ስያሜ የሰጣትን 40 ጎራሽ የጦር መሳሪያ ሰርቷል፡፡

በዛሪማ ግንባር በመገኘት ሙከራ ስለማድረጉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በፊትም ሸጉጥ ሰርቶ የተሳካ ሙከራ ስለማድረጉም ነው የተናገረው፡፡

ትምህርቱንም ከ7ኛ ክፍል በላይ መቀጠል እንዳልቻለ ያነሳው ይህ ወጣቱ፥ ራሱን በራሱ እንደሚያስተዳድርና ቤተሰብ የማገዝ ሃላፊነት እንዳለበትም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል፡፡

አሸባሪውን ህወሓት ተፋልመን እስከመጨረሻው እናስወግደዋለን የሚለው ወጣት፥ መሳሪያውንም ለዚሁ አገልግሎት ለማዋል ማሰቡን ተናግሯል፡፡

ድጋፍ የሚያደርግልኝ ባገኝ ከዚህ በላይ መስራት እችላለሁም ይላል ወጣት አብነት ወዳጄ፡፡

በሰላም አስመላሽ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.