Fana: At a Speed of Life!

400 ሺህ ሜትሪክ ቶን የመጠባበቂያ ምግብ እህል ግዢ ተፈጽሟል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን የመጠባበቂያ ምግብ እህል ግዢ መፈጸሙን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬት እንደገለጹት፥በሀገሪቱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል መጠባበቂያ የምግብ እህል በ8 ማዕከላዊ መጋዝኖች ውስጥ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚውል 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን መጠባበቂያ የምግብ እህል ግዢ መፈጸሙን ነው የተናገሩት።
ከዚህ ውስጥም 72 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥40 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሚሆነው ደግሞ ወደብ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል።

ቀሪው የምግብ እህልም እስከ ፊታችን ታህሳስ ወር ድረስ ተጓጉዞ ሀገር ውስጥ በሚገኙ ማከማቻ መጋዝኖች ይሰራጫል ነው ያሉት።

በቅርቡም ተጨማሪ 300 ሺህ ሜትሪክ ቶን መጠባበቂያ የምግብ እህል ለመግዛት አስፈላጊው የግዢ ሂደት መጀመሩን ተናግረዋል።

በህወሓት ወረራ ምክንያት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን ያስታወሱት አቶ ደበበ፥ ለእነዚህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት እና ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም በአማራ ክልል ባህርዳር እና አፋር ክልል ሰመራ ከተሞች አስቸኳይ የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች መቋቋማቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በህወሓት ቁጥጥር ስር ለሚገኙ አካባቢዎችም በዓለም የምግብ ፕሮግራም አማካኝነት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.