Fana: At a Speed of Life!

በህወኃት ውስጥ ያለው ቡድን የሀገር መከላከያ ጦር ጄት መትቼ ጥያለሁ ሲል የገለጸው ፍጹም ሀሰት ነው – ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወኃት ውስጥ ያለው ቡድን የሀገር መከላከያ ጦር ጄት መትቼ ጥያለሁ ሲል የገለጸው ፍጹም ሀሰት መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ገለጹ።

ሜጀር ጄኔራል መሐመድ አየር ኃይሉ አሁንም ቢሆን የተመረጡ ቦታዎችን ማጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት።

የጥፋት ቡድኑ በመከላከያ ኃይል እየደረሰበት ባለው ጥቃት በርካታ ይዞታዎችን እየለቀቀ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

ሜጀር ጄኔራሉ በርካታ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎችም በሰላም እጃቸውን እየሰጡ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.