Fana: At a Speed of Life!

441 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 47 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4670 የላቦራቶሪ ምርመራ 441 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 127 ሺህ 227 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 47 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 113 ሺህ 21 ሆኗል።

እንዲሁም የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 966 ደርሷል።

በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ 12 ሺህ 238 ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 226 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 836 ሺህ 527 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.