Fana: At a Speed of Life!

ፋሲል ከነማ ፕሪምየር ሊጉን በድል ሲጀምር ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል፤
ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ዛሬ ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከሰበታ ከተማ ያለግብ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሙጅብ ቃሲም በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ 44ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ነገ እሁድ ከቀኑ 4 ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ የሚጫወት ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከሰዓት በኋላ ባለው ፕሮግራም 9 ሰዓት ላይ ጅማ ከተማ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታድየም ይገናኛሉ።

እንዲሁም ሰኞ ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ወላይታ ዲቻ ከሀዲያ ሆሳዕና፤ ቀን 9 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ፡፡

ሁሉም ጨዋታዎች በአዲስ አበበ ስታዲየም ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.