Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ኳታር የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ኳታር ንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በዶሃ ሊካሄድ ነው።

ፎረሙ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የልምድ ልውውጥ የሚያጠናክር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከሶስት ሳምንት በኋላ የሚካሄደው ፎረም በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ይደረግበታል።

በፎረሙ ላይ ግብርና እና ማምረቻውን ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገቧ ተጠቅሷል።

የመንገድ መሰረተ ልማትን ጨምሮ በመርከብ እና የመገናኛ መሠረተ ልማት ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበች ሃገር መሆኗ ተጠቁሟል።

በኳታር ከ22 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ምንጭ፦ www.gulf-times.com/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.