Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች 3 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህግ ማስከበር ዘመቻው ለተፈናቀሉ የአማራ ክልል ዜጎች 3 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሠለሞን ፍስሀ እንደገለፁት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ድጋፎች ተደርገዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በአጠቃላይ 3 ሺህ ኩንታል ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ ኩንታል ጤፍ ፣ 1 ሺህ ኩንታል ስንዴና 1 ሺህ ኩንታል በቆሎ የምግብ እህል መሆኑን ነው ኮሚሽነር ሰለሞን ያስረዱት፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ በክልሉ ህዝብ ስም አመስግነዋል፡፡

ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ አያይዘውም አስተዳደሩ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በቅንጅት ህግ ላስከበረው የአማራ ልዩ ሀይል ከዚህ በፊት ያደረገው ድጋፍ የሚመሰገን እና አስተዳደሩ ከጎኑ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.