Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ የባንክ አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት በመቐለ ከተማ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ዛሬ ከሰአት ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።
ይህን ተከትሎም ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸው ታውቋል፡፡
የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው ከንቲባው ተናግረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.