Fana: At a Speed of Life!

52 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአንድ ሳምንት ብቻ 51 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ31 ሚየን ብር በላይ የሚገመተው ወደ ሀገር ሲገባ ሲሆን ከ20 ሚሊየን  ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ነው ተብሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የቁም እንስሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ጌጣጌጥ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና አደንዛዥ ዕፅ ይገኙበታል፡፡

በከፍተኛ መጠን ከተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ በሞያሌ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ነጌሌ ቦረና፣ ቡሌሆራ መስመር አድንዛዥ ዕፅ፣ በሀዋሳ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ጢጢቻ፣ ጪጩ፣ ኮንሶ፣አዳባ፣ ዲላ መስመር ዘጠኝ ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ስጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ ናቸው፡፡

እንዲሁም በሞያሌ ቅርንጫፍ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ እንዲሁም በድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀረር፤ ድሬደዋ፣ ለጋር፣ ቢዮቆቤና ደወሌ መስመር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ  የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

እንዲሁም በባህርዳር ቅርንጫፍ ሰራቫ፣ ሻውራ፣ መተማ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 30 የብሬይን ጥይት፣ 166 የክላሽ ጥይት፣ 2 ሺህ 771 የአሜሪካን ዶለር በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስቴሩ ሁሉም ከተባበረ ለህገ-ወጦች የፋይናንስ ምንጭ የሚሆነውን የኮንትሮባንድ ንግድ በመግታት የሀገር ሰላምና ፀጥታ ማረጋገጥ ይቻላል ብሏል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.