Fana: At a Speed of Life!

530 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኮሪያ ዓለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ድጋፍ አደረጉ።

530 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ለመከላከያ ሚኒስቴር፣ ለፌዴራል ፖሊስ ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ለክልል ዋና ከተሞች እና ድጋፍ ለሚሹ ለመቆዴኒያ ድጋፍ አድርጓል።

ለዚህም 18 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በሁለተኛ ዙር በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ተመራዎች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በጋራ እንደሚያቀርቡ ተነግሯል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማትም ለድጋፉ ምስጋና አቅርበዋል።

 

በፈትያ አህመድ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.