Fana: At a Speed of Life!

58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ባደረገው ፍተሻ ነው 46 ነጥብ 6 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡
የገቢ ኮንትሮባንዱን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አዳማ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ፣ 8 ነጥብ 4 እና 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻላቸው ተመላክቷል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ÷ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.