Fana: At a Speed of Life!

6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ እየተሰራ ነው – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፤ ፍትሃዊ እና ግልፅ እንዲሆን ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ሀገራዊ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሬይ ፌልትማን እና የአሜሪካ ሴናተሮች ምርጫውን ነፃ፤ ፍትሃዊ እና ግልፅ ለማድረግ ምርጫን በማራዘም መሰረታዊ ለውጥ እንዲካሄድ በጽሁፍ ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ በዳብዳቤ መልስ ሰጥቷል፡፡

ግንቦት 28/2013 ዓ.ም የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ከጅምሩ ጀምሮ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን በዳብዳቤው መግለጹን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው 49 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 48 ፓርቲዎች የወከሉ 9ሺህ እጮዎቻቸውን ማቅረባቸውን፣ ከ190 በላይ ሀገር አቀፍ የሲቪክ ባህበረሰብ ድርጅቶች መራጮችን ማስተማራቸውን ፣32 ሀገር አቀፍ ተቋማት ምርጫውን ለመታዘብ ፍቃድ ወስድው እየሰሩ ስለመሆናቸው ቦርዱ አስታውቋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና እጩዎቻቸው በምርጫው ሂደት ገንቢ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ያስታወቀው ምርጫ ቦርድ፣ በመላ ሀገሪቱ የምርጫው ስራ ለመምራትም ከ100ሺህ በላይ የምርጫ አስፈፃሚዎች በመንቀሳቀሰ ላይ ናቸው ብሏል፡፡

የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ ከመቼውም ጊዜ በላይ በግልፅነት እየተመራ መሆኑን ያስታወቀው ቦርዱ፣ ከዚህ በፊት በነበሩት ሀገራዊ ምርጫዎች የነበረውን የታዓማኒነት ችግሮች ለመቅረፍም የሚያስችል ስራ መሰራቱንም አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምርጫው ለመካሄድ ሌላ አዲስ ሪፎርም እንዲደረግ የቀረበው ሀሳብም ከወጪም ሆነ ከጊዜ እና ከሌሎች ጉዳዮች አንፃር የሚመከርና የሚመረጥ አካሄድ አይደለም ብሏል ቦርዱ፡፡

በመሆኑም ሀገራዊ ምርጫውን ለማካሄድ እስካሁን የተካሄዱ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የምርጫ ህግጋቶች አክብረው ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ቦርዱ ጠይቋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በዩ ኤስ አይ ዲ አማካኝነት ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለው የዴሞክራሲ ሸግግር እያደረገ ላለው ዘርፍ ብዙ ድጋፍም ምርጫ ቦርድ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት እውን እንዲሆን የአሜሪካ ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባሰራጨው ደብዳቤ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.