Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ዙር ሃገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ዙር ሃገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዕውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ በአንድ ማዕከል አገልግሎት የተሻለ ስራ የሰሩ ተቋማት እና ባለሙያዎች፣ የላቁ የኢንተርፕራዞች፣ የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸው የአነስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት፣ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚህም 80 ኢንተርፕራይዞች፣ ሶስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ሶስት የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርጉ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እውቅና አግኝተዋል።
ባለፉት ወራት ለ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ተብሏል።
በምስክር ስናፍቅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.