Fana: At a Speed of Life!

6ኛው የብዙሃን ስፖርት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስድስተኛው ዙር የብዙሃን ስፖርት መርሃ-ግብር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።

አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ከተማ እና ህብረተሰብ መፍጠርን ዓላማ ባደረገው በዚህ ሁነት በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የዛሬውም የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ለአዲስ አበባ አረንጓዴነት የድርሻዬን እወጣለሁ በሚል መሪ ቃል ነው የተከናወነው።

እንደ አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን መረጃ በከተማዋ በስልሳ ስድስት የመንግስት ትምህርት ቤቶች የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው።

በዛሬው የብዙሃን ስፖርት  የተለያዩ ስፖርት ማህበራት ፣ የኢትዮጵያ ቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ፣ አትሌቶች ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.