Fana: At a Speed of Life!

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያን የነገ እጣ የሚወስን ነው – አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያን የነገ እጣ የሚወስን ነው ሲሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ።
ምንም እንኳን የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም ለሀገሪቱ ሲባል ልዩነትን አቀራርቦና አጣጥሞ ሀገርና ህዝብ የሚመራ መንግስትን መመረጥ እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት፡፡
በደቡብ ክልል ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ያነሱት አቶ ርስቱ ህዝቡ የሚፈልገውን ለመምረጥ የምርጫ ካርድ እያወጣ ነው ብለዋል ።
በክልሉ ባሉ 7 ሺህ 848 የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች እየተመዘገቡ መሆኑን በመጥቀስ ለምርጫ ሂደቱ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የክልሉ ኑዋሪዎችም መብታቸውን ለመጠቀም ካርድ እያወጡ መሆኑን ተናግረዋል።
በጌታሰው የሽዋስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.