Fana: At a Speed of Life!

650 ፓትሮል ተሸከርካሪዎች ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተበረከቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 650 ፓትሮል ተሸከርካሪዎች በዛሬው ዕለት ተበርክተዋል።
 
የፀጥታ ስራ የማስከበር ሂደቱን ለመደገፍ የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ተሽከርካሪዎችን ማስረከቡ ተነግሯል።
 
ለኮሚሽኑ የተደረገው ድጋፉ የክልሉን የፖሊስ ሀይል በማሻሻል ፀጥታን ለማስከበር የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያግዝ መነገሩን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን  በስነ ምግባርና ሠላምን በዘላቂነት በማስፈን ረገድ ሚና ለነበራቸው አባላት የእውቅናና ማእረግ እድገት ሰጥቷል።

በአዳማ አባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ ከረዳት ሳጂን እስከ ምክትል ኮሚሽነር የሚደርስ የማዕረግ እድገት መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.