Fana: At a Speed of Life!

628 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 333 የላቦራቶሪ ምርመራ 628 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 118 ደርሷል።
በ24 ሰዓታቱ 868 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 44 ሺህ 506 ደርሷል።
እንዲሁም ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ የተገለፀ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 384 መድረሱ ተጠቁሟል።
ቫይረሱ ካለባቸው 45 ሺህ 226 ሰዎች መካከል 303 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.