Fana: At a Speed of Life!

649 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 185 የላቦራቶሪ ምርመራ 649 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ 740 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ባለፈም የ11ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 745 መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 960 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 79 ሺህ 579 መድረሱም ተገልጿል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 664 ሺህ 375 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል፡፡
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 31 ሺህ 414 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 313 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.