Fana: At a Speed of Life!

74 አባላት ያሉት የእስራኤል የልዑካን ቡድን ጎንደር ከተማ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 74 አባላት ያሉት የእስራኤል የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ታሪካዊቷን ጎንደር ከተማ ገብቷል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
 
በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።
 
የልዑካን ቡድኑ መሪ ያቆብ አጉል በበኩላቸው÷ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልጸው÷ የተጀመረውን የሁለቱን ሀገራት የህዝብ- ለህዝብ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት በጎንደር ከተማ ቆያታቸው የተለያዩ ታሪካዊ ቦታዎችን የሚጎበኙ መሆኑን ከጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.