Fana: At a Speed of Life!

89 አለም አቀፍ ጋዜጠኞች 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመዘገብ ፍቃድ አግኝተው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ግዜ 89 አለም አቀፍ ጋዜጠኞች 6ኛውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ለመዘገብ ፍቃድ አግኝተው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ።
አሃዙ እስከ አሁን ምርጫውን ለመዘገብ ፍቃድ ያገኙ የውጭ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ብዛት ብቻ መሆኑንና በቀጣይም ጥያቄ አቅርበው ለመዘገብ የሚገቡትን ዝርዝር ይፋ እንደሚያደርግ ባለስልጣኑ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ ጋዘጠኞቻቸውን የወከሉ የውጭ ሚዲያዎች ቢቢሲ፣አልጀዚራ፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ሮይተርስ፣ ኤ.ኤፍ.ፒ፣ ቪ.ኦ.ኤ፣ ኤ.ፒ፣ ዶቼ ዌሌ፣ ፈይናንሻል ታይምስ፣ ስካይ ብሮድካስቲንግ፣ ከዮዶ ኒውስ፣ አውስታራሊያን ብሮድካስት፣ ዴት ዜይት፣ ዬሌ ብሮድካስት፣ ዣይስ ኒውስ፣ ፍራንክፈርት ሩንዶሽ፣ ዜድ ዲ. ኤፍ ጀርመን ቲቪ፣ ናሽናል ፕብሊክ ሬዲዮ (ኤን ፒ.አር)፣ ቬሪጀስ ሬዲዮ፣ ጃፓን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ስዊድን ደጀንስ፣ ዴር ስተርን፣ ፊኒሽ ብሮድካስቲንግ፣ ትሮው ሚዲያ፣ አሽራቅ ኒውስ ሰርቪስ፣ ኖርዊጂያን ብሮድካስቲንግ፣ ኤጅንሲያ ኤፍ ኤም፣ ሲ.ኤን.ኤን እና ሲ.ቢ.ኤስ መሆናቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያሳያል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.