Fana: At a Speed of Life!

94 በመቶ ኢትዮጵያውያን የኮቪድ19 ክትባትን ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው – የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ክትባት ደህንነት ከተረጋገጠ እና ስኬታማ ከሆነ 94 በመቶ ኢትዮጵያውያን ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ እንደሆኑ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ማወቁን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) አስታወቀ።

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል እና የለንደን የንፅህና እና የትሮፒካል ህክምና ትምህርት ቤት በጋራ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ደህንነት ከተረጋገጠ እና ስኬታማ ከሆነ በአፍሪካ የህዝቡ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል የሚል የዳሰሳ ጥናት አካሂደዋል።

በዚህም በአብዛኛው 79 በመቶ የሚሆኑት ክትባቱ ደህንነቱ ከተረጋገጠ ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናቸውን በጥናታቸው አመላክተዋል።

ከነሃሴ እስከ ታህሳስ ወር በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከኢትዮጵያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኮቲ ዲቯር፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋቦን፣ ኬንያ፣ ማላዊ፣ ሞሮኮ፣ ኒጄር፣ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ እና ኡጋንዳ 15 ሺህ ሰዎች ተሳትፈዋል።

በጥናቱ መሰረት ክትባቱን ከመውሰድ ጋር ተያይዞ ከሀገር ሀገር እና በአምስቱ የአፍሪካ ቀጠናዎች ልዩነት እንዳለ ታይቷል።

በዚህም በጥናቱ ከተሳተፉት ኢትዮጵያውያን 94 በመቶዎቹ እና በኒጀር 93 በመቶዎቹ ውጤታማ ክትባት ከሆነ ለመውሰድ ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል።

በሌላ በኩል በሴኔጋል 65 በመቶዎቹ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 59 በመቶዎቹ ብቻ ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ እንደሆኑ ታውቋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል 18 በመቶዎቹ ክትባቱን ሙሉ በመሉ ደህንነቱ የተረጋገጠ አይደለም ብለው የሚያምኑ ሲሆን 25 በመቶዎቹ ደግሞ የኮቪድ 19 ክትባቶች ደህንነታቸው ያልተጠበቀ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ጥናቱ አመላክቷል።

ጥናቱ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና ክትባት ጋር ተያይዞ የማህበረሰቡን እውቀት እና ግንዛቤ ለመመርመር ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል።

በመሆኑም የእውቅት ክፍተት፣ ባህላዊ እምነቶች እና ክትባቱ በመሰራጨቱ ሊኖሩ የሚገቡ መረጃዎችን በጥናቱ መለየት እንደተቻለ ተነግሯል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.