Fana: At a Speed of Life!

96 ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 96 ኢትዮጵውያን በዛሬው ዕለት ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የቆዩ መሆናቸውን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በታንዛኒያ ኢሪንጋ በሚባለው ግዛት በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ የነበሩ 104 ኢትዮጵውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

እንዲሁም በቅርቡ ሞሮጎሮ፣ ሩቩማ፣ ንጆም፣ ቤምቤያ እና ሶንግዌ በሚባሉ የታንዛኒያ ግዛቶች ታስረው የነበሩ 294 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.