Fana: At a Speed of Life!

96 ኪሎግራም የሚመዝን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ቁስና አደገኛ እፅ ወደ ውጪ ሊወጣ ሲል ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 96 ኪሎግራም የሚመዝን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ቁስና አደገኛ እፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ሊወጣ ሲል ተያዘ፡፡
 
በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ በኩል ደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ በሚበር አውሮፕላን ብዛታቸዉ 39 የሆነ 44 ኪሎ ግራም የሚመዝን ጠፍጣፋ ኖራ የሚመስል አደንዛዥ እፅ በፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡
 
በተመሳሳይ ብዛቱ 42 የሆነ 52 ኪሎ ግራም በድምሩ 96 ኪሎግራም የሚመዝን ለግዜው ለመለየት ግልፅ ያልሆነ ጠፍጣፋ ኖራ የሚመስል ንጥረ ነገር ተይዟል።
 
ኢዜአ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ÷የተያዘው አደገኛ እጽ በፌደራል ፖሊስ በምርመራ እንዲጣራ ከተላከ በኋላ፤ በውጤቱ አደገኛ እፅ እንደሆነ ተረጋግጧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.