የሀገር ውስጥ ዜና

ከአሉባልታዎች በላይ ኢትዮጵያ ዛሬም የኢንቨትመንቶች አይን ማረፊያ ናት – ኢ/ር ታከለ ኡማ

By Meseret Awoke

November 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሉባልታዎች በላይ ኢትዮጵያ ዛሬም የኢንቨትመንቶች አይን ማረፊያ መሆኗን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ከአውስትራሊያ፣ ስዊድን፣ ካናዳ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና የጣሊያን የማዕድን ኩባንያዎች ጋር ሰፊና ገንቢ ውይይቶች ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ÷ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሏቸውን ኢንቨስትመንቶች ከማሳደግ አልፈው ተጨማሪ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋልም ነው ያሉት፡፡

አክለውም ‘’በኛ በኩል ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ከስምምነት ደርሰናል’’ ብለዋል፡፡

ውይይቱ ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንቶችን የመሳብ አቅም እንዳለው ያረጋገጠ ተጨማሪ ማስረጃ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሁሉም ግንባር ትግላችን ይቀጥላል ፤ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ብለዋል ኢንጂነር ታከለ በመልዕክታቸው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!