የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደግንባር መዝመት ለአፋር ህዝብ ትልቅ መልዕክት አለው – አይሻ መሀመድ

By Meseret Awoke

November 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደግንባር መዝመት ለአፋር ህዝብ ትልቅ መልዕክት እንዳለው የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መህመድ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ “የአፋር ተጋድሎ እና አገር የማዳን ጥሪ” በሚል ርዕስ ጉደይ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የአፋር ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መዝመት ኢትዮጵያ መሪ የሚዘምትላት አገር መሆኗን ይበልጥ የተረዳበት እንደሆነ አንስተዋል፡፡

የአፋር ህዝብ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መነሳቱን ገልጸዋል፡፡

ወራሪው ቡድን በክልሉ በሴቶች፣ ህጻናት፣ ሃይማኖት አባቶች ላይ ያደረሰውን ጥፋት ገልጸው÷የአፋር ህዝብ አሸባሪውን ቡድን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው መሆኑንም ኢንጂነር አይሻ ጠቁመዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!