የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ዘርፉን የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥርዓት ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

By Meseret Awoke

November 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የመረጃ፣ የተግባቦትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አተገባበር ሥርዓትን ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዩኔስኮ እና ሁዋዌ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር “ቴክኖሎጂ የትምህርት ቤት ሥርዓት ለሁሉም ምቹ እንዲሆን ያስችላል” በሚል መሪ ቃል የፕሮጀክቱን ሥራ ማስጀመሪያ መድረክ አካሂዷል።

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ለማሳካት አዎንታዊ ጥረት ከተስፋፋ በመጀመሪያው ምዕራፍ ትግበራ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል።

ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት ሁሉም የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ ጥረትና በትልቅ ኃላፊነት እንደሚሰራ ይጠበቃል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፥ ፕሮጀክቱ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አተገባበርን ለማሻሻል የሚተጉ የልማት አጋር አካላትን በተለይም የግል ዘርፉን እንደሚያበረታታ ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቱ ጥራትን ለማሻሻልና አካታች የሆነ የትምህርት ፍትሃዊነትን በማንኛውም ጊዜና ቦታ ያለማቋረጥ ለማዳረስ ያለመ ነው መባሉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!