አዲስ የኮቪድ 19 ዝርያ በመምጣቱ በርካታ የአለም ሃገራት በወረርሽኝ እየተመቱ በመሆኑ ክትባቱን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ያሳሰቡት ሚኒስትሯ ÷ ባለፉት ሁለት ሳምንት እየተሰጠ በሚገኘው የክትባት ዘመቻ እስካሁን ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የክትባት ዶዝ መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡
አዲስ የኮቪድ 19 ዝርያ የሆነውን “የኦሚክሮን” ቫይረስ ለመከላከል በመግቢያ በሮችና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የነበሩ ቁጥጥሮችን የማጥበቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ እስካሁን ከ6 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።