የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ስርዓቱን ሃገር ገንቢ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

By Feven Bishaw

December 01, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ስርዓቱን ሃገር ገንቢ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እርስ በእርስ እንዳንተማመን ያደረገን ስርዓት ጊዜው አብቅቶ “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” ለማድረስ በሙሉ አቅማችን ወደ ስራ የምንገባበት ጊዜ ተቃርቧል ብለዋል።