Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪው ህወሓት አባላትም ሆኑ የዘረፉት ንብረት ከአማራ ክልል እንዳይወጡ ሕዝቡ እርምጃ እንዲወስድ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ ፣አበባ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተደመሰሰ ያለው የአሸባሪው አና ወራሪው ህወሓት አባላትም ሆኑ የዘረፉት ንብረት ከአማራ ክልል እንዳይወጡ ሕዝቡ እርምጃ እንዲወስድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጥሪ አቀረቡ።
 
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ዶክተር ይልቃል በመግለጫቸው፥ መንግሥት ላቀረበው የክተት ጥሪ ከሕዝቡ የተሰጠው ምላሽ ፈጣን እና አበረታች በመሆኑ ምስጋና አቅርበው፥ የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
 
በ “ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” እየተመዘገበ ያለው ድል የመላው ኢትዮጵያውያን መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።
 
መንግሥት እየወሰደ ባለው የማጥቃት እርምጃ አሸባሪው ህወሓት በሁሉም ግንባሮች እየተደመሰሰ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ሕዝቡ ከጸጥታ ኅይሉ ጋር በመቀናጀት ይህንን ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ቡድን እንዲቀብረው መልጽክት አስተላልፈዋል።
 
አንድም የሽብርተኛው ህወሓት ቡድን አባል ከወረራቸው አካባቢዎች አምልጦ እንዳይወጣ ሕዝቡ መንገዶችን በመዝጋት እንዲደመስሰውም ጠይቀዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ አባላት የዘረፏቸው ንብረቶች እንዳይወጡም ማህበረሰቡ በንቃት መከታተል እና ማስጣል አለባት ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
የሀገርን ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማስከበር ወጣቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና ልዩ ኅይልን እንዲቀላቀልም ዶክተር ይልቃል ጥሪ አስተላልፈዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.