Fana: At a Speed of Life!

የአራዳ ክ/ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለከተማ ከህዝብ ያሰባሰበውን ከ12 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የእለት ደራሽ ምግቦች ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቧል።
 
የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት የበሰሉ ምግቦችና የታሸገ ውሃ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ተበርክቷል።
 
በማዕድ ማጋራቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ÷ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች ድል እያስመዘገበ ኢትዮጵያን እየታደጋት ስለሆነ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
 
የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስከበር ጁንታውን እየሰባበረ እየገሰገሰ ካለው የመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን የህልውና ድጋፍ ይቀጥላልም ነው ያሉት።
 
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችም ከመከላከያ ጎን በግንባር በመሠለፍ ደጀንነታቸውን እንደሚያስቀጥሉ ምክትል ከንቲባው አረጋግጠዋል።
 
በታለ ማሞ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.