ስፓርት

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ  የኩዌት ሊግ ውድድሮችን ለመምራት ወደ ስፍራው ያቀናሉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 02, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ  በኩዌት ሊግ ውድድሮችን ለመምራት መመረጣቸውን ተከትሎ ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናሉ፡፡

 

የኩዌት እግር ኳስ ማህበር ሰሞኑን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ÷  ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከህዳር 2 – 13 በኩዌት ኤስ ቲ ሲፕሪሜሪሊግ  የሚደረጉ ጨዋታዎችን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ በጠየቁት መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄዉን በመቀበሉ ነው ወደ ስፍራው የሚያቀኑት፡፡

 

በዚሁ መሰረት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ማምሻውን ወደ ስፍራው እንደሚያመሩ  ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡