የሀገር ውስጥ ዜና

ሸዋሮቢት ከተማ የመብራት አገልግሎት ማግኘት ጀመረች

By Meseret Awoke

December 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሽብር ቡድኑ ነጻ የወጣችው ሸዋሮቢት ከተማ የመብራት አገልግሎት ማግኘት መጀመሯን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ ነጻ በወጡ አካባቢዎች አስቸኳይ ጥገና እያደረገ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ስራ አስኪያጅ አቶ ማህተሜ አለሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዚህም ሸዋ ሮቢት ከተማ ሙሉ በሙሉ መብራት ስታገኝ ደብረ ሲና አካባቢ የሚገኙት አርመኒያ አስፍቸውና ጭራ ሜዳ አካባቢ የተባሉ ቦታዎች መብራት ማግኘታቸው ተገልጿል።

ደብረ ሲና መብራት እንድታገኝ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ማህተሜ÷ በቅርብ ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ትሆናለች ብለዋል።

ተቋሙ ነጻ የወጡ አካባቢዎችን በቶሎ አገልግሎት ለመስጠት ይሰራል ያሉት ስራ አስኪያጁ÷ ቡድኑ በንብረት ላይ ያደረሠው ጥፋት ተጠንቶ በቅርቡ ይፋ ይሆናልም ነው ያሉት።

በከድር መሀመድ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!