ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና እና አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

December 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

የአየር ንብረት ለውጥ በተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳር እንዲሁም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰ መሆኑ ይነገራል።

በመሆኑም በዳካር በተካሄደው 8ኛው የቻይና – አፍሪካ የትብብር የሚኒስትሮች ፎረም ላይ÷ ቻይና እና አፍሪካ በጉዳዩ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ሰነድ አዘጋጅተዋል፡፡

የቻይና አፍሪካ ትብብር ጉባኤ በፈረንጆቹ 2000 መካሄድ የጀመረ ሲሆን÷ በሥነ – ምህዳርና አካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ያደረገ መርሃ ግብር ነው፡፡

በደን እና በሥነ-ምህዳር ጥበቃ፣ ዘላቂ የተፈጥሮ ሐብት አጠቃቀም እና የኃይል አቅርቦት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ በአካባቢ መሠረተ – ልማት ግንባታ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በዱር እንስሳት ጥበቃ እንዲሁም በርሃማነትን በመከላከል ላይ ጉባኤው ውይይት ያደረገባቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን የዘገበው ሲጂቲ ኤን ነው፡፡