ስፓርት

ማንቸስተር ዩናትድ አርሴናልን 3 ለ 2 አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

December 03, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ትላንት ምሽት በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናትድ አርሴናልን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ቡሩኖ ፈርናንዴዝ  እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲያስቆጥሩ÷ የአርሴናልን ሁለት ጎሎች ስሚዝ ሮዉ እና ማርቲን ኦዲጋርድ አስቆጥረዋል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ሶስት ደረጃዎችን በማሻሻል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷አርሴናል አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የነጥብ ልዩነታቸዉም ወደ ሁለት መጥበብ ችሏል፡፡

በሌላ የእንግሊዝ ፕሪሜሪሊግ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ብሬንት ፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ጎሎችን ካኖስ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር ሰን ሁዊንግ ሚን ሁለተኛዉን ጎል አስቆጥሯል፡፡