ስፓርት

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Tibebu Kebede

February 13, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ሞገስ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሞገስ ታደሰ በአዳማ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሲዳማ ቡና፣ በወልዲያ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision