Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት ጥቃት አለመፈጸሟን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች በሚል የቀረበባትን ውንጀላ አስተባበለች።

በቅርቡ ሩሲያ በኢድሊብ ግዛት ፈጽማዋለች በተባለው ጥቃት በጥቂቱ የ14 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው የሶሪያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

እንደ ድርጅቱ ገለፃ በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ንጽሃን ዜጎች ውስጥ ሰባቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ነበሩ።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ሞስኮ የተባለውን ጥቃት አልፈጸመችም ሲል አስተባብሏል።

በቀጠናው እንደ አዲስ ያገረሸው ቀውስም ቱርክ የሚጠበቅባትን ሃላፊነት በተገቢው ሁኔታ ባለመወጣቷ የተፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቱርክ በአካባቢው ያለው ቀውስ ይበልጥ እንዲባባስ የሚያደርግ የጦር መሳሪያ በሀገራቱ ድንበር እንዲገባ ትፈቅዳለች ሲልም ኮንኗል።

ስለሆነም በቀጠናው የሚስተዋለውን ቀውስ በዘላቂት ለመፍታት በህገ ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር ላይ ቁጥጥር ከማድረግ ባለፈ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችን እና ተቃዋሚዎችን መለየት እንደሚገባ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በተያያዘ ዜና በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ በአሜሪካ ወታደሮች እና በሀገሪቱ መንግስት ታማኝ ወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

ግጭቱ የመንግስት ታማኝ ወታደሮች በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር ወደ አካባቢው እንዳይገባ በመከልከላቸው ምክንያት የተፈጠረ መሆኑም ተገልጿል።

 

ምንጭ፦  ሺንዋ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.