Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል እየሰበሰቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፣ የጎንደር እና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን ሰብል እየሰበሰቡ ነው፡፡
 
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማረሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ምልምል ኮንስታብሎች እና የዋናው መስሪያ ቤት አመራርና ሰራተኞች በአሌልቱ ወረዳ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
 
በተመሳሳይ የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ሰራተኞችና የህግ ታራሚዎች በባሶና ወረና ወረዳ በአባሞቴ ቀበሌ የዘማች አርሶ አደሮችን የደረሱ ሰብሎች ሰብስበዋል፡፡
 
የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ቀጸላ ደበበ÷መምሪው የህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ ከሚያደርጋቸው የደጀንነት ተጋባራት ውስጥ የሚሊሻ አርሶ አደሮችን ሰብል መሰብስብ አንዱ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በዚህ መሰረትም 167 የሚሆኑ የህግ ታራሚዎችና 36 የመምሪያው ሰራተኞች የተሳተፉበት ሰብል ስብሰባ ተካሂዷል ነው ያሉት፡፡
 
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞችም የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ደጀንነታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
 
ሰራተኞቹ የአገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር በግንባር ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እየተፋለሙ የሚገኙ ዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰ በኩል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ጥሪ ማቅረባቸውን ከተቋማቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.