የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በዱባይ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ሀገሪቱ በቀጠናው የምትከተለውን የስራ ስምሪት አቅጣጫ ለመወሰን ይረዳል- አምባሳደር ሱሌይማን

By Tibebu Kebede

February 13, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዱባይ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት ውይይት በቀጣይ ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ የምትከተለውን የስራ ስምሪት አቅጣጫ ለመወሰን እንደሚረዳ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ወደ ተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ያቀኑ ሲሆን፥ በቆይታቸውም በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መብት እና ጥቅም የሚያስከብሩ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።