የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ የመንገድ ደህንነት እና ኢንሹራንስ ፈንድ አገልግሎት ደንብ በመጠናቀቅ ላይ ነዉ – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

By Meseret Awoke

December 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አዲስ የመንገድ ደህንነት እና ኢንሹራንስ ፈንድ አገልግሎት ደንብ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ፡፡

ወ/ሮ ዳግማዊት በትዊተር ገጻቸዉ ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት አዲስ የመንገድ ደህንነት እና ኢንሹራንስ ፈንድ አገልግሎት ደንብ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ ከመንገድ ፈንድ ክፍያዉ ቢያንስ አምስት በመቶው ለድህረ-ድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ወጭዎች የሚመደብ ነዉ ብለዋል።

ይህም ከመንገድ ደህንነት ጋር በተያዘ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ተጨማሪ ፋይናንስ ለማግኘት ይረዳል ነው ያሉት፡፡

ለአፍሪካ እና ሌሎች ታዳጊ የአለም አገራት የመንገድ ደህንነት ትልቅ ትኩረት መስጠት አማራጭ ሳይሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ሚንስትሯ፥ በኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነት ላይ መስራት ወጪ ሳይሆን ወሳኝ ኢንቨስትመንት ነውም ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!