ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ አቻ ተለያዩ  

By Tibebu Kebede

February 13, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ ፍቅረየሱስ ተክለብርሀን በ29ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

የወልቂጤ ከተማን ግብ ደግሞ አህመድ ሁሴን ጨዋታው በተጀመረ 10ኛው ደቂቃ ላይ ኳስን ከመረብ አገናኝቷል።