ዓለምአቀፋዊ ዜና

አዳማ ባሮው በጋምቢያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ

By Melaku Gedif

December 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳማ ባሮው በትንሿ ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ጋምቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተደረገው የሁለተኛው የስልጣን ዘመን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አሊዬ ሞማር ንጃይ እሁድ እለት የመጨረሻውን ውጤት ለጋዜጠኞች ይፋ ካደረጉ በኋላ ባሮው አሸናፊ መሆናቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ባሮው በምርጫው 53 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸናፊ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

የእርሳቸው የቅርብ ተቀናቃኝ የሆኑት ኦሳይኑ ዳርቦ ከባሮው 28 በመቶ ያነሰ ድምጽ ማግኘታቸውም ተመላክቷል።

ዳርቦ እና ሌሎች ሁለት እጩዎች ሂደቱ የአሰራር ግድፈት አለበት በማለት ውጤቱን እንደማይቀበሉ መግለጻቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!