አሸባሪው ህወሃት በጋሸናና በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ ዜጎችን በጅምላ ጨፍጭፏል- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሃት በጋሸናና በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
እነዚህ ጥቃቶች የአሸባሪ ቡድኑን ትክክለኛ ማንነት የገለፁ ናቸው ብለዋል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ።
አሸባሪ ቡድኑ በአፋርና በአማራ ክልል የፈፀማቸው ወንጀሎች ጀኖሳይድ የሚለውን ቃል የሚገልፁ ናቸው ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ ዜጎችን በጅምላ ረሽኗል፤ የጅምላ መቃብሮችም ተገኝተዋል ነው ያሉት።
ሆኖም በጭና፣ በአጋምሳ፣ በጋሊኮማ፣ በውርጌሳ፣ ውጫሌ እና በርካታ አካባቢዎች የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ለሰብዓዊ መብት ቆመናል የሚሉ አገራትና ተቋማት ድምፃቸውን ማጥፋታቸውን አንስተዋል።
ዲያስፖራውና ዜጎች ይሄንን እውነት ለማሳወቅ መስራት አለባቸውም ብለዋል።
በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም መንግስት ሁኔታውን እያጤነ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያነሱት።
በአፈወርቅ እያዩ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!