የሀገር ውስጥ ዜና

በጭፍራ አሸባሪው ህወሓት አረመኔያዊ ድርጊት ፈፅሟል- ነዋሪዎች

By Meseret Awoke

December 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በጭፍራ የሃይማኖት ተቋማትን ደፍሮ ርኩስነቱን አሳይቷል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገለጹ፡፡

አሸባሪው ቡድን ንጹሃንን ገድሏል ፤ ነዋሪዎችን አፈናቅሏል፤ ከግለሰብ ቤቶች እስከ ትላልቅ ተቋማት ድረስ ከፍተኛ ዝርፊያ እና ውድመት ፈፅሟልም ነው ያሉት ነዋሪዎቹ።

ይህም ሳያንሰው የሃይማኖት ተቋማት ላይ ጉዳት በማድረስ ይህ ቀረ የማይባል አረመኔያዊነቱን በግልጽ አሳይቷል ብለዋል፡፡

ወራሪው ቡድን ቁልፍ ቦታ ብሎ ከያዛቸው ቦታዎች አንዷ በሆነችው ጭፍራ በመነሳት የሚሌን መስመር በመቆጣጠር የአዲስ አበባ ጅቡቲን መስመር እዘጋለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ ውስጥ እንደነበረ አንስተዋል።

ይህ ብቻ ሳይሆን ህልሙን ለማሳካት ቡድኑ በከተማው ውስጥ ከባድ መሳሪያዎችን ሲጠቀም እንደነበር ነዋሪዎች በስፍራው ቅኝት ላደረገው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!