የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በከሚሴ እና ኮምቦልቻ የግለሰብና የመንግስት ንብረቶችን በተደራጀ መንገድ መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

By Meseret Awoke

December 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ በከሚሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በቆዩባቸው ጊዜያቶች የግለሰብ እና የመንግስት ንብረቶችን በተደራጀ መንገድ መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ፋብሪካዎችን፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን መዝረፋቸውን እና ማውድማቸውን ነው የገለፁት።

እንደዚሁም ለሰብአዊ ድጋፍ የተቀመጡ እህሎችም በሽብር ቡድኖቹ ተጭነው መወሰዳቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ከንብረት ዘረፋው በተጨማሪ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንደተፈጸመባቸውም ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት።

አሸባሪዎቹ በኮምቦልቻ ከተማ ማንነትን መሰረት በማድረግ ነዋሪዎችን ገድለዋል፤ ዘርፍዋል።

በከሚሴም እንዲሁ ብዙ ጥፋት ማድረሳቸውን ገልጸው፥ ቡድኖቹ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል ተወላጆችን እርስ በእርስ ለማጋጨት ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነው ለረጅም ዓመታት በመተሳሰብ እና በፍቅር የኖርን ህዝቦች በመሆናችን ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!