የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ

By Mekoya Hailemariam

December 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሰድስት ጎረቤት አገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት  ከጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ እንደምትሰጥም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት።