ፋና ስብስብ

ጃፓናዊው ቢሊየነር ወደ አለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ ተጓዙ

By Meseret Awoke

December 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኦንላይን ፋሽን ከፍተኛ ሃብት ያካበተው እና ለህዋ ምርምር አድናቂ እንደሆነ የሚነገርለት ጃፓናዊው ባለሃብት ዩሳኩ ማዛዋ እና ፕሮዱሰሩ ዮዞ ሂራኖ በግላቸው ወጪ ያደረጉት ይህ የጠፈር ጉዞ በ10 አመታት ውስጥ ከተደረጉት ጉዞዎች የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

ቢሊኒየሩ ማዛዋ ከበረራ በፊት በተደረገ የዜና ኮንፈረንስ እንደተናገሩት ምድርን ከጠፈር ላይ ሆኜ ማየት እፈልጋለሁ፣ ክብደት የሌለኝ አይነት ስሜት እንዲሰማኝም እፈልጋለሁ ሲል ተደምጧል፡፡

በተጨማሪ ከዚህ የጠፈር በረራ በኋላ ምን አይነት ለውጥ እንደሚኖረኝ ለማወቅ ጓጉቻለሁ ብሏል ቢሊየነሩ ።

ባለሃብቱ ዩሳኩ ማዛዋ እና ፕሮዱሰሩ ዮዞ ሂራኖ በጣቢያው ላይ ለ12 ቀናት ቆይታ ያደርጋሉ ነው የተባለው።

ባለሃብቱ ለዚህ የጠፈር ጉዞ ያወጡት ወጪ አልተገለጸም መባሉን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!